← All tools

FilePort editorial

Latest news

Updated 12d ago

380 stories
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል - ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ‼️
News Aug 5, 2026 · 34d ago

ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል - ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ‼️

ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡፡ የአየር ኃይሉ የ3ኛ አየር ምድብ ላስመዘገበው የላቀ የግዳጅና የሥራ አፈጻጸም ስኬት በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው የምድቡ ጠቅላይ መምሪያ የእውቅናና የምስጋና መርሐ…

News Aug 4, 2026 · 34d ago

የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናን 81 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም ተባለ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ክልላዊ ፈተና 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጿል።ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ 48 እና ከዛ በላይ ማለፊያ ነጥብ ተቆርጦለታል።የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመውሰድ የተመዘገቡ ተማሪዎች 86 ሺህ 502 እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን 78…

#እንድታውቁት 2
News Aug 4, 2026 · 35d ago

#እንድታውቁት

በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆኖ በሚቆይበት…

ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የወንዶች አልባሳትን የሰረቁ 6 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ 8
News Aug 4, 2026 · 35d ago

ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የወንዶች አልባሳትን የሰረቁ 6 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 9 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 መቻሬ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ተጠርጣሪዎቹ ደብሩ መለሰ፣ ሞገስ ተካይ፣ ብርሃኑ አያሌው፣ ዘሪሁን በለጠ፣ ሚሊዮን መስፍን እና አብዱልሰላም ነስረዲን የተባሉ ሲሆኑ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B 40762…

በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️
News Aug 4, 2026 · 35d ago

በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️

በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ  እንደገለጹት…

ለኔታንያሁ ወንድም ሐውልት‼️
News Aug 4, 2026 · 35d ago

ለኔታንያሁ ወንድም ሐውልት‼️

ኡጋንዳ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ወንድም ሐውልት አቆመች። የኡጋንዳ የጦር አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ወንድም የሆኑት ዮናታን ኔታንያሁን የመታሰቢያ ሐውልት ኡጋንዳ በሚገኘው የኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አሮጌ ተርሚናል ላይ አስመርቀዋል። ዮናታን…

ሳይታጠብ እስከ አንድ ወር የሚቆይ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ቀረበ 2
News Aug 4, 2026 · 35d ago

ሳይታጠብ እስከ አንድ ወር የሚቆይ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ቀረበ

አሜሪካዊው የልብስ ኩባንያ ‘ሄርክሊዮን’ ያለ ምንም እጥበት እስከ አንድ ወር ድረስ መጥፎ ጠረን ሳይይዝ በየቀኑ መልበስ የሚያስችል "HercShirt V5.0" የተሰኘ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል። ኩባንያው ለዚህ ፈጠራው መዳብ፣ ብር፣ ዚንክ፣ ወርቅ እና የእሳተ ገሞራ አመድን ጨምሮ ሰባት ልዩ ንጥረ…

የአነስተኛ ገንዘብ ኖቶች እጥረት‼️
News Aug 4, 2026 · 35d ago

የአነስተኛ ገንዘብ ኖቶች እጥረት‼️

የአነስተኛ የገንዘብ ኖቶች እጥረት የችርቻሮ ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን እየፈተነ ይገኛል። ​በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ አነስተኛ የገንዘብ ኖቶች በተለይም የ 10 ብር ኖት እጥረት በዕለታዊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው። በርካታ የሱቅ ባለቤቶች መልስ በማጣታቸው ምክንያት ደንበኞችን…

በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር ተነገረ
News Aug 4, 2026 · 35d ago

በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር ተነገረ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምቹ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል። ከእነዚህም መካከል አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት  አገልግሎት በኤምባሲዎችና በቆንስላዎች በኩል በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጿል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ…

ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ
News Aug 4, 2026 · 35d ago

ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

#TECNO_SPARK_50
News Aug 4, 2026 · 35d ago

#TECNO_SPARK_50

አዲሱ የቴክኖ ስፓርክ 50 ስልክ ጥርት ያለ ስክሪኑ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም ወይንም ፎቶ እና ቪዲዮችን ኤዲት ለማድረግ 120 Hz ፈጣን እና 6 ነጥብ 78 ኢንች ስክሪኑ ፍጥነት እና ጥራትን አብሮ ይሰጦታል፡፡ ይሄ ዘርፈ ብዙ ስልክ ያለ ምንም ጥርጥር…

በራያ ውጥረት አለ-ነዋሪዎቹ
News Aug 4, 2026 · 35d ago

በራያ ውጥረት አለ-ነዋሪዎቹ

ከቀናት በፊት በሱዳን አዋሳኝ ሸረሪና በፌደራል ኃይሎች እና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል የነበረው ግጭት ጋብ ቢልም፣ በራያ አላማጣ ግንባር በኩል ግን ወታደራዊ ዝግጅቱ እና ፍጥጫው ማየሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ፣ የህወሓት ሠራዊት በራያ ግንባር በጨርጨር፣በቢሶበር እና…

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
News Aug 4, 2026 · 35d ago

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 672 ኢትዮያውያን በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺህ 670 ወንዶች፣ 1 ሴት፣ 1 ጨቅላ ሕፃን እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 34 ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5 ቀን 2018…

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማረፊያ የሚሆን መሬት ሰጠች
News Aug 4, 2026 · 35d ago

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማረፊያ የሚሆን መሬት ሰጠች

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የትራንስፖርት ኮሪደር ለማዘመን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ ስምምነት በመተግበር በሞጆ ከተማ የመሬት ርክክብ ፈጸሙ። ላለፉት 25 ዓመታት ዘግይቶ የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ ለጅቡቲ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታ የሚውል መሬት ለጅቡቲ…

ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
News Aug 3, 2026 · 36d ago

ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ

በአምቦ ከተማ ውስጥ ደህንነት ነኝ በማለት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ መቀጣቱ ተገልጿል ።የአምቦ ከተማ  ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ተከሳሽ ዘሪሁን ጉርሙ የሰላሳ ዓመት ግለሰብ ነው።   በከተማዋ…

News Aug 3, 2026 · 36d ago

ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦ ✅ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 👉ጎጃም በረንዳ ጫፍ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ሰን ሆቴል፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ፣…

ይከፈላል ተብሏል‼️
News Aug 3, 2026 · 36d ago

ይከፈላል ተብሏል‼️

በምርጫ ቦርድ እና በምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል ያለው የክፍያ ውዝግብ። ​በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የተሳተፉ የመስክ አሠልጣኞች፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎችና የቆጠራ አስተባባሪዎች በገቡት ውል መሠረት ሊከፈላቸው የሚገባው የአገልግሎትና የጉዞ አበል ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ገለጹ። ባለሙያዎቹ ኃላፊነታቸውን በሰዓቱና…

በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
News Aug 3, 2026 · 36d ago

በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኘው በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ የርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉንና በሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ አስተዳደር መምሪያ አስታወቀ። በአደጋው በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ እና በ2 ሰዎች ላይ…

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ 2
News Aug 3, 2026 · 36d ago

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።   የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 194374 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 165342(85.06%) ተማሪዎች 50% እና…

ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት…
News Aug 3, 2026 · 36d ago

ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት…

ሳዑዲ አረቢያ ስምንት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር አዲስ ተጨማሪ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት አዋቅራለች። ከእነዚህ ስምንት ሀገራት መካከል አምስቱ ሀገራት ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ናቸው። የታቀደው ህብረት ሳዑዲ አረቢያን፣ ዮርዳኖስን፣ የመንን እና…