← All news
News Oct 19, 2026 · 19d ago

የኔታንያሁ አነጋጋሪ ካርታ‼️

ትላንትና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ስለ እስራኤል የወደፊት ደህንነት ባደረጉት ንግግር ላይ የታየው ካርታ ቴል አቪቭ በመካከለኛው ምስራቅ እና ከዚያም በላይ ያሉትን አዳዲስ የጂኦፖሊቲካዊ አሰላለፎች እንዴት እንደሚመለከት እና ማን የእስራኤል ጠላት እና ወዳጅ እንደሆነ እንዲሁም እነማንን እንደምትደግፍ ይፋ አድርጋለች። ሰማያዊ ቡድን፡የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ባህሬን፣ ህንድ፣ አዘርባጃን፣ የየመን STC፣ የሶሪያ ድሩዝ ተገንጣይ ምክር ቤት፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊላንድ፣ ፑንትላንድ፣ የሃፍታር ሊቢያ፣ ቆጵሮስ፣ ግሪክ እና የሱዳን RSF ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ደማቅ ሰማያዊ ቀለም የተሰጣት ሲሆን የእስራኤል አጋር ሀገር ተብላለች፣ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎቹ ደብዘዝ ያለ ሰማያዊ ቀለም የተሰጣቸው ሲሆን እነዚህ ወዳጅ ሀገራት በሚል ተሰይመዋል። አረንጓዴ ቡድን፡ ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ የየመን PLC፣ ቱርክ፣ ፓኪስታን፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ የሊቢያ ጂኤንዩ፣ ግብፅ፣ የዌስት ባንክ፣ ሶሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ሊባኖስ፣ ሰሜናዊ ቆጵሮስ እና ሶማሊያ ሲሆኑ እነዚህ ሀገራት ወዳጅም ጠላትም ያልሆኑ friendly በሚል ተፈርጀዋል። ቀይ ቡድን፡ ኢራን፣ የኢራቅ PMF፣ ሂዝቦላህ፣ የየመን አንሳሩላህ፣ በጋዛ ያሉ ሃማስ እና ሩሲያ ሲሆኑ እነዚህ የእስራኤል ጠላት ተብለዋል።