"አያዋጣችሁም" አብይ ለሻብያ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕግደፍ መልእክታቸውን አስተላለፉ። ጠቅላዩ ከኢትዮጵያ ቴልቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኤርትራ "ከነጻነት በኋላ" መቆርቆዟን አውስተዋል። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል በነበረችበት ወቅት ከ300 በላይ የኢንዱስትሪ ተቋማት እንደነበሯት አውስተው አሁን ግን ያ ሁሉ እንደሌለ ገልጸዋል። ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ሻብያ የተከተለው ፖሊሲ እንደሆነ ተችተዋል። "ሕግደፍ በውስጥ ጉዳይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በጎረቤቶቹ የውስጥ ጉዳይ በተለይም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመግባት ፀብ አጫሪ ድርጊት መፈጸሙን" ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ ለሻብያ አያዋጣውም፤ በዚህ ከቀጠለ እና ጎረቤታችንነትን አምኖ የማይቀበል ከሆነ እጅግ እጅግ የከፋ ነገር ይደርስበታል፤ አያዋጣችሁም" በማለት አስጠንቅቀዋል።