← All news
News Oct 19, 2026 · 20d ago

ከስልክ ስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን በጤናችን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ምንድን ነው?

በጨለማ ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ ሆኖ ረጅም ሰዓታት የሞባይል ስልክ ብርሃንን መመልከት ለዓይን ብዥታ፣ ለከፍተኛ የዓይን ድካም እና ለዘላቂ የእንቅልፍ መዛባት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።   በሳይንሳዊ እና ህክምና መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፡ ከስልኮችና ዲጂታል ስክሪኖች የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን (Blue Light) አእምሮ የእንቅልፍ ሆርሞን የሆነውን ሜላቶኒን (Melatonin) እንዳያመነጭ እንቅፋት ይፈጥራል። ይህ ሁኔታ በተለይ ማታ ማታ ስልክ የሚያበዙ ሰዎችን ለአእምሮ ድካም እና ለተዛባ የእንቅልፍ ዘይቤ ያጋልጣል።   እነዚህ ሁኔታዎች በየቀኑ በሚደጋገሙበት ወቅት የዓይን መድረቅ፣ የራስ ምታት እና የዕይታ መቀነስ ችግሮች እንደሚከሰቱ በህክምና ዘገባዎች ተመልክቷል።   የህክምና ባለሙያዎች እንደሚያስገነዘቡት ከሆነ ማታ ለመተኛት ሲዘጋጁ ስልኮችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ወይም ከዓይን እይታ ማርቅ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም የሞባይል ስልኮች ላይ የሚገኘውን የዓይን ጥበቃ (Night Light / Blue Light Filter) ሁነታን መጠቀምና ከመተኛት ከ30 ደቂቃ በፊት ስክሪን አለመመልከት መልካም እንደሆነ ተመልክቷል።