ኬንያ በጫት ጭማቂ ሕገወጥ አምራቾችን ላይ እስከ 1 ሚሊዮን ሽልንግ ቅጣት ልትጥል ነው።
የኬንያ የስታንዳርድ ቢሮ የጫት ምርትን ቀላቅለው በሚዘጋጁ መጠጦች ላይ የጥራት ማረጋገጫ ምልክትን ያላግባብ በሚጠቀሙ አምራቾች እና ነጋዴዎች ላይ ከባድ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። የጥራት ተቆጣጣሪው ቢሮ ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ በጫት ላይ የተመሰረቱ መጠጦች ወይም ንጥረ ነገሮች የጥራት ፈቃድ መርሃ-ግብሩ አካል እንዳልሆኑ እና ለእንደነዚህ አይነት ምርቶች ምንም ዓይነት የማረጋገጫ ፈቃድ እንዳልሰጠ አፅንኦት ሰጥቷል። ሆኖም ጎጂ የሆኑ የጫት ንጥረ ነገሮችን የያዙ መጠጦችን ለገበያ የሚያቀርቡ አካላት፣ ለመደበኛ ፍራፍሬ ጭማቂዎች የተሰጡ ፈቃዶችን በመጠቀም ሕገወጥ አሰራር ሲከተሉ መገኘታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል። ይህንን የሕግ ጥሰት ሲፈጽሙ የተገኙ አካላት እስከ 1 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ወይም በእስራት እንደሚቀጡ ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ሸማቾች በነዚህ መጠጦች ላይ የሚደረጉ የጥራት ማረጋገጫ ጥያቄዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ተገንዝበው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቋል።