በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 447 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
ዛሬ ጥቅምት 9/ 2019 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 447 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 139 ወንዶች ፣ 261 ሴቶች እና 47 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 47 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።