← All news
News Oct 19, 2026 · 19d ago

“ጣቶቻችን በቃታ ላይ ናቸው፤ ከእስራኤል ጋር ለሚደረገው ጦርነት ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል”- ኢራን

የኢራንና የእስራኤል ወታደራዊ ግጭት እንደገና የመቀጣጠል ስጋት እየጨመረ መሆኑ ነው። የኢራን መከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናስርዛዴህ አገራቸው ከእስራኤል ጋር ሊከሰት ለሚችል ወታደራዊ ግጭት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ስለ ወታደራዊ ዝግጅታቸው ሲናገሩ፣ “ጣቶቻችን በቃታ ላይ ናቸው፤ ከእስራኤል ጋር ለሚደረገው ጦርነት ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል” ብለዋል። መግለጫው ቴህራን ከእስራኤል ጋር ሊኖር ለሚችለው ተጨማሪ ግጭት ያላትን ወታደራዊ ዝግጁነት እና ጠንካራ አቋም የሚያመለክት ነው።