← All news
News Oct 19, 2026 · 19d ago

የስጋ ቤቶች ደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ታወቀ፡ የ“No More ስጋ” ዘመቻ ውጤት እያስገኘ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከልክ ያለፈ የስጋ ዋጋ ጭማሪ በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተጀመረው “የስጋ ዋጋ ይቀንስ - No More ስጋ” የቦይኮት ንቅናቄ በዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አቀባበል በማግኘት ላይ ይገኛል። በተለይም በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ የዲጂታል እምቢተኝነት፣ ሸማቾች የሉካንዳ ቤቶችን የዋጋ ጭማሪ ለመቃወም የወሰዱት ቀጥተኛ እርምጃ ሆኗል። በአንዳንድ ታዋቂ የስጋ ቤቶች የ1 ኪሎ ግራም ስጋ ዋጋ እስከ 6 ሺህ ብር መድረሱ የህብረተሰቡን ቅሬታ ወደ ተግባራዊ ቦይኮት እንዲቀየር አድርጎታል። ትናንት እና ዛሬ በተደረጉ የመስክ ማጣራቶች ቀደም ሲል በከፍተኛ ዋጋ ጥሬ ስጋ በሚሸጡ ታዋቂ የሉካንዳ ቤቶች አካባቢ የታየው የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። የቦይኮት እርምጃው በተግባር ውጤት ማሳየት መጀመሩን የተመለከቱ ነዋሪዎች፣ የሸማቾች አንድነት ከተጠናከረ የገበያ ግፊት በመፍጠር ዋጋውን ወደ መደበኛ ደረጃ ማመለስ እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የስጋ ፍጆታን ሙሉ በሙሉ ወይም ለጊዜው ያቆሙ ዜጎች በሰውነታቸው ውስጥ የፕሮቲን እጥረት እንዳይከሰት ስጋን በሌሎች ከፍተኛ ፕሮቲን ባላቸው ምግቦች መተካት እንዳለባቸው ባለሙያዎች መክረዋ። ስጋን መተካት የሚችሉ ዋና ዋና የፕሮቲን ምንጮች፦ 1 ምስር፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽምብራ፣ አኩሪ አተር (Soybeans) እና ሎቢዮ እንቁላል፣ አይብ፣ እርጎ እና ወተት አሳ እና የዓሳ ውጤቶች የኦቾሎኒ ቅቤ፣ የሱፍ ፍሬ፣ የኑግ ፍሬ እና የተለያዩ ለውዞች Mushrooms ስፒናች እና ብሮኮሊ እንዲበሉ ተመክሯል:: ይህ በህብረተሰቡ አብሮነት እየተመራ ያለው የቦይኮት ዘመቻ፣ ሸማቾች በገበያው ላይ ያላቸውን የመደራደር አቅም ያሳየ ትልቅ ማሳያ ነው። ገበያን ማረጋጋት የሁሉም ወገን ኃላፊነት በመሆኑ፣ ነጋዴዎችም የህዝቡን አቅም ያገናዘበ ፍትሃዊ የዋጋ ተመን ሊከተሉ ይገባል።