«ለቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች የመሬት ይዞታ መብት እና ጥቅማጥቅሞች መመቻቸታቸው ተገለጸ»
በየትግራይ ክልል አዲስ የወጣ ደንብ ለቀድሞ ተዋጊዎች እንደየተቀላቀሉበት ጊዜ የተወሰነ የመሬት መብት እና የተለያዩ ነፃ ጥቅማጥቅሞችን የሚሰጥ መሆኑ ተሰማ። በደንቡ መሠረት በ2013 ዓ.ም. የተቀላቀለ 200 ካሬ ሜትር፣ ከሰኔ 22/2013 እስከ ታኅሣሥ 30/2014 ዓ.ም. የተቀላቀለ 175 ካሬ ሜትር፣ እንዲሁም ከጥር 1/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ደንቡ መጽደቅ ጊዜ የነበረ ተዋጊ 140 ካሬ ሜትር የመሬት መብት ያገኛሉ። ለሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በየደረጃው ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በመንግሥት የሚሸፈን የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣ ቲሸርት፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ምንጣፍ አቅርቦት ይደረግላቸዋል። አባላቱ እነዚህን መብቶች የሚያገኙት «የትግራይ ሕዝብ ሰላም ዋስትና ለመሆን በተልዕኮ በመቆየት ሲቀጥሉ» ብቻ መሆኑ መደንገጉ፤ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር ከማቀላቀል እና ትጥቅ ከማስፈታት የፕሪቶሪያ ስምምነት ጋር የሚቃረን እና በወታደራዊ መስመር ለማቆየት የተሰራ ስሌት መሆኑ ተገልጿል። በሌላ በኩል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከጌታቸው ረዳ እና ከደብረጽዮን አንጃዎች ጋር በነበራቸው ተለዋዋጭ አቋም እና የውስጥ ፖለቲካዊ ውዝግቦች ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች መውጣታቸው ተመላክቷል።