← All news
News Oct 19, 2026 · 19d ago

ከ138 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 138 ሺህ 736 አዳዲስ ደንበኞችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን ገለጸ። ይህ አፈጻጸም ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ29.4 በመቶ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፣ የተቋሙን አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር 6.03 ሚሊዮን አድርሶታል። በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ 30 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፣ የአገልግሎት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ የማስፋፊያና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በሌላ በኩል ተቋሙ አሠራሩን ለማስተካከልና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል በተደረገ ማጣራት ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ 29 ሠራተኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።