30 የታሸገ ውሃ አምራቾች የአዲስ አበባ ከተማ የመሸጫ ዋጋቸውን አሳወቁ
የኢትዮጵያ መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር የ30 የታሸገ ውሃ አምራቾችን የአዲስ አበባ ከተማ የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቋል። ማኅበሩ ቀደም ሲል በጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም የ13 የውሃ አምራቾች ለአከፋፋዮች የሚያስረክቡበትን ዋጋ ፣ የአከፋፋዮችን የትርፍ ህዳግ እና አከፋፋዮች ለቸርቻሪ ነጋዴዎች የሚያስረክቡበትን ዋጋ ለቢሮው ማሳወቁ ይታወሳል። ማኅበሩ በጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ለቢሮው በላከው ደብዳቤ በአዲስ አበባ ከተማ የታሸገ ውሃ በማከፋፈል ላይ ያሉና ቀደም ሲል የዋጋ መረጃቸውን ያላሳወቁ ተጨማሪ አምራቾችን በማካተት አጠቃላይ የዋጋ ዝርዝሩን በድጋሚ ልኳል።