የኩላሊት ጠጠር እንዳለባችሁ የሚያሳዩ 5 ምልክቶች
1. ከባድ ህመም • በቀኝ ወይም በግራ ጀርባችሁ ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ህመም የሚሰማችሁ ከሆነ። ይህ ህመም ከጎድን አጥንታችሁ በታች የሚሰማ ሲሆን ወደታችኛው ሆድ ሊሰራጭ ይችላል። 2. በሽንት ውስጥ ደም ካስተዋላችሁ • በሽንት ውስጥ ደም መኖር ጠጠሩ በኩላሊት ትቦዎች ውስጥ አልፎ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ያሳያል። 3. ቶሎ ቶሎ መሽናት • ከተለመደው በላይ ወደ ሽንት ቤት መመላለስ እና ለመሽናት መፈለግ የኩላሊት ጠጠር ከፊኛ አጠገብ እንደሚገኝ ያሳያል። 4. ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ • በጣም ከባድ ህመም ሲኖር ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ይሰማችኋል። 5. ትኩሳት • ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት በኩላሊት ዉስጥ ኢንፌክሽን መፈጠሩን ያሳያል። ⚠️ እነዚህን ምልክቶች ካያችሁ ወደ ህክምና በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!