← All news
News Nov 6, 2026 · 1d ago

ሴዶ እና ንቃት ህሊና እንደሚፋለሙ አዘጋጁ በሰበር ዜና ገለፁ"

በቅርቡ በሚካሄደው የኢቲኤፍሲ 3 (ETFC 3) ውድድር ላይ የንቃት ህሊና እና የሴዶ ማርሻል አርት ፍልሚያ በይፋ መያዙን የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል አቶ ጌታቸው በሰበር ዜና ማብሰራቸው ይታወሳል። የሁለቱን ተፋላሚዎች ያለፈ ታሪክ ስንመለከተው፤ 1. ንቃት ህሊና ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ወደ ሪንግ ገብቶ አንድ አሸንፎ አንዱን ተሸንፏል። 2. ሴዶ ማርሻል አርት ወደ ሪንግ የገባው አንዴ ብቻ ሲሆን፣ ያደረገውንም ብቸኛ ጨዋታ በሽንፈት አጠናቋል። አሁን ላይ ሁለቱ ወጣቶች ለውድድሩ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ይሰማል። ነገር ግን ጉዳዩን አነጋጋሪ ያደረገው የሴዶ ነገር ነው፤ እሱ በሰጠው አስተያየት ወደ ውድድሩ ፍጹም እንደማይገባ ገልጿል። ሆኖም የስፖርቱ አድናቂዎችና ተከታዮች "ግድ ነው፣ ትገባለህ" እያሉ ግፊትና ማበረታቻ እያደረጉለት ይገኛሉ። ሁለቱ ተፋላሚዎች በሰጡት ምላሽና በድባቡ ዙሪያ የሚነሱ ነገሮች ለጊዜው የውድድሩን ትኩረት የሳቡት ሲሆን፣ ወደፊት ምን እንደሚፈጠር አብረን የምናየው ይሆናል።