← All news
News Nov 6, 2026 · 1d ago

በአዳማ ከተማ ስድስት እግርና ሁለት ራስ ያላት ድንቅ ግልገል ፍየል ተወለደች።

⚫ ፍየሏ በሁለቱም አፏ መጥባት ትችላለች! በአዳማ ከተማ ሁለት ራስ፣ ሁለት አፍ፣ ስድስት እግር እንዲሁም ሁለት የብልት አካላት በአንድ ላይ የያዘች ግልገል ፍየል ተወልዳለች። ግልገሏ በሁለቱም አፏ አተት የመጠባት አቅም እንዳላት የተገለጸ ሲሆን ከዚች ግልገል ጋር አብራ የተወለደችው ሁለተኛዋ መንታ ግን በተፈጥሮአዊ የአካላት መዋቅር የተወለደች ናት። በአዳማ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት የእንስሳት ጤና ቡድን መሪ ዶክተር ደሪቤ ሀይሉ ስለ አጋጣሚው በሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ፣ እንዲህ ዓይነቱ የሰውነት አካላት መደራረብ የሚከሰተው በእንስሳቱ የእርግዝና ወቅት የመንታ እንቁላል ክፍፍል ሂደት ከ12 እስከ 17 ባሉት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሳይለያይ ሲቀር እንደሆነ ገልጸዋል። Credit : ABS