ፓስተር ፖል ማኬንዚ በ191 ሰዎች ግድያ የ200 ዓመታት እስራት ተበየነባቸው
በኬንያ ተከታዮቻቸውን ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት በሚል በረሃብ እንዲያልቁ ያደረጉት የ191 ሰዎችን ህይወት ያጠፉት የኑፋቄ ቡድን መሪ ፖል ማኬንዚ የ200 ዓመታት እስራት ተፈረደባቸው። ፍርድ ቤቱ በማኬንዚ ላይ በግድያ ወንጀል የ100 ዓመት እንዲሁም በርሃብ በማስገደል ወንጀል የ100 ዓመት በድምሩ የ200 ዓመታት እስራት በይኖባቸዋል። ከተገደሉት ሰዎች መካከል ከአንድ ግለሰብ ውጭ ሁሉም ሕፃናት እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን ከእርሱ ጋር የተከሰሱ 28 ተባባሪዎችም እስከ 160 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ማኬንዚ እ.ኤ.አ. በ2023 በሻካሆላ ደን ውስጥ ከ400 በላይ አስከሬኖች በጅምላ ተቀብረው ከተገኙ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ዳኛ ዲያና ሞቻቼ ውሳኔውን ሲያስተላልፉ ድርጊቱ ታቅዶ የተፈጸመ አሰቃቂ ጭካኔ መሆኑን ገልጸዋል።