ከ144 ሺህ በላይ ደንበኞች የስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ ሆኑ
ከ144 ሺህ በላይ ደንበኞች የስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ ሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በመላ አገሪቱ ለ144 ሺህ 388 ደንበኞች ዘመናዊ የኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎችን ማዳረሱን አስታወቀ። ቆጣሪዎቹ ደንበኞች በተለያዩ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች የኤሌክትሪክ ኃይል በማንኛውም ጊዜና ቦታ እንዲገዙ ከማስቻላቸውም በተጨማሪ፣ የቆጣሪ ንክኪን ለመቆጣጠርና የኃይል መቋረጥ ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዙ ተገልጿል።