«የፌዴራል ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በሁርሶ የሰጡትን ወታደራዊ ሥልጠና አጠናቀቁ፤ የክልል ፕሬዝዳንቶች ቀጣይ ተሿሚዎች መሆናቸው ተገለጸ»
በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲካሄድ የቆየውን ዉጤታማ ወታደራዊ ሥልጠና የፌዴራል ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አጠናቀው መውጣታቸው ተመላክቷል። በማሰልጠኛ ማዕከሉ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ጀነራል ይመር መኮንን፣ የፖለቲካ አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠናና ጥበብን መቅሰማቸው ይበልጥ ብቁ እና አቃፊ ውሳኔ ሰጪ መሪዎች እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሥልጠና መርሃ ግብሩ በቀጣይ የሚቀጥል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የክልል ፕሬዝዳንቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደሚገቡ ታውቋል። ይህ አሰራር የአመራር አቅምን ለማጎልበት እና የጸጥታ መዋቅሩን ግንዛቤ ለማዳበር የሚደረግ አጠቃላይ የስልጠና አካል መሆኑ ተመላክቷል። @Seledadotio