እጅግ አሳዛኝ መረጃ‼️
👉 በምሥራቅ አርሲ 34 ኦርቶዶክሳውያን መገ*ደላቸውን ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። 👉 በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስ*ከሬን በእንዳቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡን MK TV ጨምሮ ዘግቧል። 👉 ጥቃቱን ለማስቆም ወደ አካባቢው ሲያመሩ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የጥ*ቃቱ ሰለባ መሆናቸው ተገልጿል። 👉 በተጨማሪም በርካቶች መጎዳታቸው፣ የሕክምና እርዳታ ማግኘት መቸገራቸውና የንግድ ተቋማት መውደማቸው ተጠቁሟል።