«ቻይና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን የዲፕሎማሲ ውጥረት ለማስታረቅ አዲስ የሽምግልና ጥረት ጀመረች»
የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ሊው ዥያንፍን አዲስ አበባ ገብተው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ጋር ይፋዊ ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል። ይህ የዲፕሎማሲ ጉብኝት የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በቀጣናው የሚስተዋሉ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ካላቸው ዕቅድ ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። ልዩ መልእክተኛው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደ ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ግብፅ በማቅናት ቀጣናዊ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ የዘገባው ምንጮች አመላክተዋል። ቤጂንግ አቅርባቸዋለች የተባሉት የአራት ነጥብ የግጭት መፍቻ መርሆዎች በኢትዮጵያ በኩል አዎንታዊ ተቀባይነት ማግኘታቸው ተመላክቷል። @Seledadotio