← All news
News Nov 5, 2026 · 2d ago

የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በአየር፣ በየብስ እና በባህር ዘመቻዎችን መፈጸም በሚያስችል መልኩ እንደገና መደራጀቱን አስታወቀ"

​ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ በቀጠለችበት በዚህ ወቅት፤ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የወታደራዊ ዝግጁነት አቅሙን ከፍ አድርጎ ሙሉ በሙሉ እንደተዋቀረ ይፋ አደረገ። ​የባህር ኃይሉ አዲስ አደረጃጀትና ተልዕኮዎች የባህር ኃይል የሜዲያ ኃላፊ ኮማንደር ካሳሁን ኪዳኔ በሰጡት መግለጫ፣ ከለውጡ በፊት ጠፍቶ የነበረው የባህር ኃይል አሁን ላይ በምድር፣ በአየር እና በባህር ላይ የተጣሉበትን ሐገራዊ ተልዕኮዎች በብቃት መወጣት የሚችል ኃይል ሆኖ መደራጀቱን ገልጸዋል። በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚገኙ አካባቢዎች እና በሐይቆች ላይ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የተቀናጁ የጸጥታ ዘመቻዎች እየተካሄዱ መሆኑም ተመላክቷል። ​የአዛዦች ዝግጁነት እና የቀጠናው የባህር ደህንነት ፎረም የመከላከያ ሠራዊቱ የባህር ኃይል አዛዦች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። ይህ ምዕራፍ የተከተለው ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ያስተናገደችውን እና የበርካታ አገራትን የባህር ኃይል ተወካዮች ያሳተፈውን የቀጠናዊ የባህር ደህንነት ፎረም ተከትሎ ነው። በወቅቱ የባህር ኃይል ጠቅላይ አዛዥ ምክትል አድሚራል ክንዱ ገዙ አገሪቱ ወደ ባህር በር የምታደርገው ጉዞ "አይቀሬ" መሆኑን ማስታወሳቸው ይታወሳል። ​@Seledadotio