← All news
News Nov 5, 2026 · 2d ago

ከ 25ሺ በላይ ለሚሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የግልና የመንግስት ተቋማት የጥበቃ ሰራተኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

በቅድመ ወንጀል መከላከል ፣በፀጥታና ደህንነት ዙሪያ በከተማው ለሚገኙ የግልና የመንግስት ተቋማት የጥበቃ ሰራተኞች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡   የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ፣ የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለተቋማት ቅጥር ጥበቃዎችና ባለቤቶች ጋር የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ እየሰራ መሆኑን ያስታወቀው ቢሮው  ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ከ25000 በላይ ለሚሆኑ የኤጀንሲ ባለቤቶችና የጥበቃ ሰራተኞች በሁለት ዙር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል። አቶ ተስፋዬ ደንደር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንደገለፁት ስልጠናው በሁለት ዙር በሁሉም ክ/ከተሞች የግልና የመንግስት ተቋማት የጥበቃ ሰራተኞች የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል። የፊታችን ቅዳሜ ለሚጀመረው ስልጠና አስመልክቶ ከሰላምና ጸጥታ ሀላፊዎች፣ ከፌደራልና ከአዲስ አበባ ፓሊስ አመራሮች፣ ከግል ጥበቃ ኤጀንሲ ባለቤቶችና ከዘርፉ ሙያተኞች ጋር በማስፈጸሚያ እቅዱ ላይ የጋራ ውይይት በማድረግ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።