← All news
News Nov 5, 2026 · 2d ago

“ግብፅ በናይል ወንዝ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ስታቀርብ ለቆየችው ክርክር ኢትዮጵያን ይቅርታ ልትጠይቅ

ይገባል”- የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ግብፅ በናይል ወንዝ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ስታቀርብ ለቆየችው ክርክር ኢትዮጵያን ይቅርታ ልትጠይቅ እንደሚገባ ተናገሩ። ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ ውሃ በዘላቂነት እንዲፈስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች። በመሆኑም ግብፅ የኢትዮጵያን አስተዋጽኦ ከመቃወም ይልቅ እውቅና ልትሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የሚኒስትሩ አስተያየት በአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በውሃ ሀብት ላይ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ለረጅም ጊዜ ከቆየው አለመግባባት ጋር የተያያዘ ነው። ኢትዮዺያ ለአመታት በግንባታ ላይ የቆየው የታላቁን የኢትዮዺያ ህዳሴ ግድብ አጠናቃ ማስመረቋ ይታወቃል፤ ግብፅ ከጅማሮ አንስቶ እስከ አሁን የአባይን ውሃ በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎቷን በተለያዪ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ስምምነት ህጎች ሽፋን ከሱዳን ጋር በማበር ተደጋጋሚ ክስ እያቀረበች ነው።