← All news
News Nov 5, 2026 · 2d ago

«የሱዳን መንግሥት ለአዲስ አበባ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ በአጸፋዊ ሁኔታ በገዳሪፍ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ዘጋ»

​በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ መሻከሩን ተከትሎ፣ ካርቱም በምሥራቅ ገዳሪፍ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ማስተላለፏ ተመላክቷል። ​የሱዳን ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ይህ የአጸፋ እርምጃ የመጣው ኢትዮጵያ በአሶሳ የሚገኘውን የሱዳን ቆንስላ ሠራተኞች ከሀገር ማባረሯን ተከትሎ ነው። ​የሱዳን ጦር ባለፈው ማክሰኞ ከኢትዮጵያ ግዛት የተነሳ ድሮን በብሉ ናይል አካባቢ መመታቱን ማስታወሱ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ አገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚያቀርቧቸው የታጣቂዎች እና የድሮን ድጋፍ ውንጀላዎች መቀጠላቸው ተገልጿል። ​እ.ኤ.አ. በ2015 ለሁለትዮሽ ትብብር ተብሎ የተከፈተው የገዳሪፍ ቆንስላ መዘጋት፣ በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች መሆኑ ተመላክቷል።