ዘሌንስኪ የአሜሪካ ዲሞክራቶች በምርጫ ማሸነፋቸው ለዩክሬን ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስገኝ ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ
«ሪፐብሊካኖችንም አመሰግናለሁ፤ ነገር ግን ዲሞክራቶች ዩክሬንን ስለመደገፍና እርዳታ ስለመስጠት በግልጽ ይናገራሉ» ብለዋል ፕሬዝዳንቱ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፤ዲሞክራቶች በዚህ ሳምንት በተካሄደው የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ ያገኙት ድል ከሩሲያ ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ለኪቭ ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስገኝ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። ለጀርመኑ ህዝባዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ዘሌንስኪ በአሜሪካ ድምፅ አሰጣጥ የሚመጡ ለውጦች ለዩክሬን ጥቅም እንደሚሰሩ ተስፋቸውን ገልጸው፤ ኪቭ ቀደም ሲል የሁለቱም ፓርቲዎች ድጋፍ ነበራት ብለዋል። «ሪፐብሊካኖችንም አመሰግናለሁ፤ ነገር ግን ዲሞክራቶች ዩክሬንን ስለመደገፍና እርዳታ ስለመስጠት በግልጽ ይናገራሉ» ብለዋል። በተጨማሪም ዘሌንስኪ ዲሞክራቶች የአሜሪካ እና የአውሮፓ ግንኙነትን እንደገና ስለማደስ ያነሱትን ንግግር በማጉላት ዩክሬን የበለጠ ድጋፍ የምታገኝበት የኃይል ሚዛን ይፈጠራል የሚል ተስፋን አሳይተዋል። የዘሌንስኪ አስተያየት የተሰጠው ማክሰኞ ዕለት ከተካሄደው የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ በኋላ ሲሆን፤በዚህም ዲሞክራቶች በሴኔት እና በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር በማግኘት የሪፐብሊካኖችን የኮንግረስ ቁጥጥር እንዲያበቃ አድርገዋል፡፡ ከድምፅ አሰጣጡ በኋላ ትራምፕ፤ አስተዳደራቸውን ለማደናቀፍ እስካልሞከሩ ድረስ በኮንግረስ ከሚገኙ ዲሞክራቶች ጋር አብረው መስራት እንደሚችሉ ጠቁመዋል