ከአርሲ የድረሱልን ጥሪ‼️
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑ ታውቋል። በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ በሆነችው እንደቶ ቀበሌ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውናል። ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በተቀሰቀሰውና እየተካሄደ ባለው በዚህ ጥቃት ሳቢያ በርካታ ሰዎች ጉዳት አስተናግደዋል። በአካባቢው አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የወደቁት የቀበሌው ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት አስቸኳይ ድምፅ እያሰሙ እና አፋጣኝ የመንግሥትና የጸጥታ አካላት ምላሽ እንዲሰጧቸው «የድረሱልን» ጥሪ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተገልጿል።