← All news
News Nov 5, 2026 · 2d ago

«በአስመራ ቤተ መንግሥት ውስጥ ውጥረት ማሻቀቡ ተሰማ፤ የኤርትራ ከፍተኛ የጦር መሪዎች በፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ላይ ያላቸው አመኔታ እየመነመነ መምጣቱ ተገለጸ»

​«ሆርን ሪቪው» ባወጣው አዲስ የፖለቲካ ትንታኔ መሠረት፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ትልቁ ስጋታቸው ከውጭ ከሚመጡ ተቃዋሚዎች ይልቅ ለዘመናት አብረዋቸው የሠሩት የጦር እና የደህንነት ከፍተኛ ኃላፊዎች መሆናቸው ተመላክቷል። ​በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ፣ ማለቂያ የሌለው ብሔራዊ ውዴታ አገልግሎት እና ሥልጣንን በአንድ አካል ብቻ መጠቅለል በከፍተኛ ጄኔራሎች ዘንድ ጥልቅ ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል። ​የጦር መሪዎቹ የፕሬዚዳንቱን መቀጠል ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለራሳቸውም ህልውና ስጋት አድርገው ማየታቸውን የጠቆመው ትንታኔው፣ ነባሩን ሥርዓት ለማስቀጠል ሲባል ውስጣዊ የሥልጣን ለውጥ (መፈንቅለ መንግሥት) ሊከሰት እንደሚችል አመላክቷል። ​ከዚህም በተጨማሪ የሕወሓት ጄኔራሎች ተጨማሪ ጦርነትን በመቃወም ራሳቸውን ማግለላቸውን እና አክራሪ አመራሮች ወደ አስመራ እያፈገፈጉ መሆኑን የዘገባው ምንጮች ማሳየታቸው ተመላክቷል። ​@Seledadotio