← All news
News Nov 4, 2026 · 3d ago

ኢትዮጵያ ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ሮይተርስ ዘግቧል። እንደዘገባው ከሆነ ዲፕሎማቶቹ ሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ በሚገኘው የሱዳን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ይሰሩ የነበሩ ናቸው። ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በኋላ አዲስ አበባ ከአስመራ እና ካርቱም ጋር ያላት ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል። ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ይገኙ የነበሩ 10 የኤርትራ እና አንድ የግብጽ ዲፕሎማቶች መባረራቸው ይታወሳል። ይህን ውሳኔ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ስታቋርጥ ግብጽ በበኩሏ በኢትዮጵያ ላይ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃ ነበር። ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው በአንዳቸው የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።