ኩላሊቱን ለመሸጥ በማሰብ የ 12ዓመቱ ታዳጊ ህይወት እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቁርባኖ ቀበሌ ቀመሌ በተባለ ልዩ ስፍራ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው። ተከሳሽ ከድር ገረሙ የተባለ ሲሆን ህዳር 2ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7ሰዓት አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር እየተጫወተ የነበረውን የ12 ዓመት ታዳጊ የሆነውን አብዱልካፍ አብዱልጀሊልን በማታለል ከጓደኞቹ ለይቷ እንደወሰደው ተገልጿል። ተከሳሽ የታዳጊውን ኩላሊት አውጥቶ ለመሸጥ በማሰብ በቢላ በመውጋት ህይወቱን እንዲያልፍ ካደረገ ብኋላ ሁኔታዎች አልመቻች ሲለው በፍጥነት ከአካባቢው መሰወሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በዚህም የጉራጌ ዞን ዓቃቤ ሕህ በተከሳሹ ላይ በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ በመመስረት ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል።