← All news
News Nov 4, 2026 · 3d ago

በታዳጊ ሀገራት መካከል ያለው ንግድ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱን የዓለም ንግድ ድርጅት ገለጸ

በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል የሚደረገው ንግድ  በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ንግድ ድርጅ እና የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ-ደቡብ ትብብር ቢሮ በጋራ ባወጡት አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል።   "Transformative Partnerships for Trade Resilience" በተሰኘው በዚህ ሪፖርት መሠረት፣ በ2025 በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል የተደረገው የሸቀጥ ኤክስፖርት 7.2 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም የአለም አጠቃላይ የሸቀጥ ኤክስፖርት 27.8 በመቶ ይሸፍናል። ከ20 ዓመታት በፊት ይህ ድርሻ 14.3 በመቶ ብቻ ነበር።   ሆኖም ግን ይህ የንግድ ዕድገት አሁንም ቢሆን በእስያ ታዳጊ ሀገራት ላይ የተከማቸ ሲሆን፣ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ እና በካሪቢያን አካባቢዎች ሰፊ የክልላዊ ንግድ ትስስር ዕድሎች አሁንም ጥቅም ላይ እንዳልዋሉ ጥናቱ አመልክቷል፡፡