← All news
News Nov 4, 2026 · 3d ago

ለኢትዮጵያ መንግሥት በመሰለል የተከሰሰው ትውልደ-ኢትዮጵያዊው የአሜሪካ ዜጋ ጥፋተኛነቱን አመነ!

-እስከ 22 ዓመት የእስራት ቅጣት ሊጠበቀው ይችላል የቀድሞው የአሜሪካ መንግሥት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮንትራክተር እና ትውልደ-ኢትዮጵያዊው የአሜሪካ ዜጋ አብርሃም ተክሉ ለማ፣ እጅግ ምስጢራዊ የሆኑ የአሜሪካ ብሔራዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለማስተላለፍ በመዶለት የቀረበበትን ክስ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም. አምኗል። ይህም እስከ 22 ዓመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣው ይችላል።