← All news
News Nov 4, 2026 · 3d ago

የኤችአይቪን ስርጭት ይገታል የተባለዉ መድኃኒት ለ120 አገራት ሊቀርብ ነው‼️

የአሜሪካው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመውጋት የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችለውን "ሊናካፓቪር"  የተባለ መድኃኒት አጸደቀ። ይህም መድኃኒቱ በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 120 አገራት በዝቅተኛ ዋጋና በፍጥነት እንዲደርስ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል። የመድኃኒቱ አምራቾችና የጤና ተቋማት እንዳስታወቁት፣ መድኃኒቱ በእነዚህ አገራት ለአንድ ሰው በዓመት 40 ዶላር ገደማ የሚቀርብ ሲሆን፣ ይህም በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ከሚወሰዱ የመከላከያ እንክብሎች ዋጋ ጋር እኩል ነው ተብሏል። በየቀኑ መድኃኒት መውሰድ ለሚረሱ ወይም ለሚቸገሩ ሰዎች ይህ ክትባት ከፍተኛ መፍትሔ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን፣ ተደርገዋል በተባሉ ጥናቶችም አዳዲስ የኤችአይቪ ኤችአይቪ የመያዝ አጋጣሚዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማስቀረቱ ተረጋግጧል። Via capital