«ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ የአሜሪካን የኮሎራዶ የኮንግረስ መቀመጫ በማሸነፍ ታሪክ አስመዘገበች»
የ29 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊት እና የዴሞክራቲክ ሶሻሊስት ፓርቲ አባል የሆነችው ሜላት ኪሮስ፣ በኮሎራዶ ግዛት 1ኛ የኮንግረስ ዲስትሪክት በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ መሆኗ ተመላክቷል። ይህ ድል ሜላት ኪሮስ ያንን ግዛት ወክላ ወደ ኮንግረስ የተመረጠች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት እንዲሁም ራሷን በሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም የምትገልጽ ቀዳሚዋ ተወካይ እንድትሆን አስችሏታል። በወጣቷ መሪ አሸናፊነት ዙሪያ የተሰሙ መግለጫዎች በፖለቲካው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት የሳቡ ሲሆን፣ ድሉ ለቀጣናው እና ለዲያስፖራ ማኅበረሰቡ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ ተገልጿል።