← All news
News Nov 4, 2026 · 4d ago

ቴዲ አፍሮ የማዲንጎ አፈወርቅን አዲስ አልበም በማስመልከት ለወላጆቹ የክብር በግ ላከ::

በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ እጅግ ውብ፣ ልብ የሚነካ እና የመከባበርን ጥግ ያሳየ አስደናቂ አጋጣሚ ተከሰተ! ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በሕይወት በሌለበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ የሆነው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ያሳየው ወደር የሌለው የሰው ልጅ ፍቅርና ታላቅ አጋርነት የመላውን ሕዝብ ቀልብ ስቦ የብዙዎችን ዓይን በእንባ አርሷል። የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ የሙዚቃ አልበም መውጣቱን በማስመልከት፣ ቴዲ አፍሮ የክብርና የትህትና ምልክት የሆነ ውብ ነጭ በግ በመያዝ የማዲንጎን ወላጆች ቤት ድረስ በአካል በመገኘትና በመጠየቅ አስደናቂ ታሪክ ሰርቷል። የልጃቸውን እግር ተክቶ ሁልጊዜም እንደ አባትና እናት እየተመላለሰ የሚያጽናናቸውን ቴዲ አፍሮን ያዩት የማዲንጎ ወላጆች፣ በተሰማቸው ጥልቅ ድስታና ስሜት በረከት የታጀበ ልብ የሚነካ እናታዊና አባታዊ መርቃቸውን እንዲህ ሲሉ አፍሰዉለታል፦ «ቴዲየ፣ ሁልጊዜ ጠያቂያችን ነህ! ልጃችን ማዲንጎ ከተለየን ጀምሮ አንድም ቀን ሳታቋርጥ በየጊዜው ትጠይቀናለህ። ዛሬም የክብር በግ ልከህ ጠይቀኸናል… ዕድሜ ይስጥህ! ልጆችህንና ውድ ባለቤትህን ፈጣሪ ይጠብቅልህ!» በካናዳ የሚኖረው የማዲንጎ ታናሽ ወንድም ያሬድ አፈወርቅም ቢሆን በወንድሙ ማጣት የደረሰባቸው ሀዘን ከባድ ቢሆንም፣ የቴዲ አፍሮ ቅንነትና ክብር ግን ቤተሰቡን እንዳበራው በመግለጽ፦ «ትንሹ ሲንቅህ ትልቁ ያከብርሃልና፣ ለእኛ ላሳየኸን ወገናዊ ፍቅርና ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን!» ሲል አክብሮቱን ገልጻል። በአርቲስቶች መካከል ያለው ይህ ዓይነት ጥልቅ ፍቅር፣ ታላቅነትና እውነተኛ አጋርነት በእርግጥም ለሁሉም ትውልድ ትልቅ ትምህርትና ኩራት ነው!