የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ቀናት መቅረታቸውን አሳሰበ
ቢሮው የደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋዮች ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. በኋላ በኦንላይን የሚቀርብ የሂሳብ መዝገብ ፍጹም እንደማይቀበል አስታውቋል። ግብር ከፋዮች በተዘረጋው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በፊት የሂሳብ መዝገባቸውን አቅርበው ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጥሪ ቀርቧል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታቸውን በማይወጡ አካላት ላይ ቢሮው ባለው መረጃ በመመስረት ግብሩን ከነቅጣቱ አስልቶ ክፍያ እንዲፈጸም የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።