← All news
News Nov 3, 2026 · 4d ago

እስራኤላዊው ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ የሩሲያ ዘመናዊ

ጄቶችን መታጠቋን አስመልክቶ ምን አሉ? "የኢትዮጵያ አየር ኃይል መጠናከር   በግብፅ በኩል ሥጋት ፈጥሯል" ኢትዮጵያ ከሩሲያ የተቀበለቻቸው 12 ዘመናዊ የሱ-35 (Su-35) 4ኛ++ ትውልድ ተዋጊ ጄቶች የሀገሪቱን ወታደራዊ አቅም እና በቀጣናው ያላትን ሚና በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉት ተገለጸ። የእስራኤሉ ቻናል 14 ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ ኤዲ ኮሄን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሩሲያ ተገኝተው የተረከቧቸው እነዚህ የጦር ጄቶች ኢትዮጵያ ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም በእጅጉ እንደሚያጎናጽፏት አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህ ታሪካዊ ስኬት ኢትዮጵያ የነበሩባትን መሰናክሎች በዲፕሎማሲያዊ ጥረቷ እና በጠንካራ ዓለም አቀፍ ግንኙነቷ በመሻገር ስትራቴጂካዊ ጥቅሟን ማስከበር መቻሏን በግልጽ ያሳያል። እንዲህ ያሉ ዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ቀዳሚ መሆኗ፣ ሀገሪቱ የጠላት ጥቃትን የመከላከልና የማክሸፍ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ እንድታጠናክር አስችሏታል። እስራኤላዊው ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ ኤዲ ኮሄን እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መጠናከር በግብፅ በኩል ትልቅ ሥጋት መፍጠሩን የግብፅና የዐረብ መገናኛ ብዙኃን በቅርበት እየተከታተሉት ይገኛሉ። ተመራማሪው አክለውም፣ ግብፅ ቀጣናዊ ለውጦችን የሚመጥን ግልጽ የፖለቲካ ራዕይ እንደሚጎድላት ጠቅሰው፤ እየጨመረ የመጣው የውስጥ ኢኮኖሚ ውጥረት እና የፖለቲካ ፈተናዎች የግብፅን አመራር አገሪቱን የመምራት ብቃት ላይ ጥያቄዎች እያስነሱ መሆኑን ገልጸዋል።