← All news
News Nov 3, 2026 · 4d ago

የኢትዮጵያ ቡና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና የዲኤችኤል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ የቡና ዘርፋን ማሳደግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል። በሁለቱ ተቋማት መካከል የተመሰረተው ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን የቡና ዘርፍ ለማጠናከር፣የቡናላኪዎችን እና በዘርፋ የተሰማሩ ድርጅቶችን ወጪ ንግድ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። እንዲሁም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ቡና በአለምአቀፍ ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ለሀገር ውስጥ የቡና ንግድ ድርጅቶች አዳዲስ የገበያ እድሎችን ለመፍጠር ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሏል።የዲኤችኤል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዲርክ ቫን ዶርን በዚህ ወቅት እንተናገሩት"የኢትዮጵያ ቡና ጠንካራ ዓለም አቀፍ ፍላጎትን እያገኘ ነው። ሆኖም ግን፣ በጉምሩክ መስፈርቶች ላይ የሚደረጉ ለውጦች እና የቁጥጥር ደረጃዎች ለሚያድጉ ንግዶች የገበያ ተደራሽነት እንቅፋቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ ነው ያሉት።ስለ ዓለም አቀፍ ንግድ እና ስለ ድንበር ተሻጋሪ ሂደቶች እውቀትን ማጠናከር ላኪዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲወዳደሩ እና ወደ አዳዲስ ገበያዎች እንዲስፋፉ ያስችላቸዋል ብለዋል። የዲኤችኤል ኤስፕረስ ኢትዮጵያ ካንትሪ ኮሜርሺያል ማናጀር አቶ ዮናስ ስብሀት ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩትም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ቡናን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማድረስ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ሂደቱን አስተማማኝ ለማድረግ ያግዛል። አያይዘውም ተቋሙ የቡና አምራቾች እና ላኪዎች የቡናን ጥራትና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አሰራርን እንዲያውቁ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።