← All news
News Nov 3, 2026 · 4d ago

የታሸጉ ውሃዎች የአከፋፋዮች እና የቸርቻሪ  የመሸጫ ዋጋ  ይፋ ሆኗል በዚህም ሁለት ሊትር  ከ40 እስከ 50 እንዲሸጥ ተተምኗል

በአዲስ አበባ ከተማ የታሸጉ የውሃ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በተመለከተ የታሸገ ውሃ አምራቾች በማህበራቸው በኩል ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቀዋል። በሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ማንኛውም ነጋዴ የሚሸጣቸውን ምርቶች ዋጋ በሚታይ ቦታ የመለጠፍ/ለሸማቾች የማሳወቅ ግዴታ የሚጥልበት እንደመሆኑ መጠን ዋጋቸውን ያላሳወቁ የውሃ አምራች ፋብሪካዎች በሁለት ቀናት ውስጥ ዋጋ እንዲያሳውቁ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቋል። ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የታሸገ ውሃ አምራቾች  ጋር በተደረሰው የጋራ መግባባት መሠረት የመሸጫ ዋጋቸውን ያሳወቁ ፋብሪካዎችን እንዲሁም ማህበሩን አመስግነዋል። ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአዋጁ መሠረት የመሸጫ ዋጋቸውን ያላሳወቁ የውሃ አምራች ድርጅቶች ውሃዎችን በመዲናዋ መቸርቸር እንደማይችሉ ገልፀው በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያሳውቁ አሳስበዋል። ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ በመዲናችን አዲስ አበባ ውሃ በቦቴ እያዞሩ የሚሸጡ ድርጅቶችን በተመለከተ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመነጋገር መፍትህ እንደሚሰጥበት አሳውቀዋል። በመጨረሻም የታሸጉ ውሃዎች ዝርዝር ዋጋ ከዚህ ልጥፍ ጋር የተያያዘ ሲሆን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የቁጥጥር ሠራተኞች ፋብሪካዎቹ ባሳወቁት ዋጋ መሠረት ሽያጭ እየተፈፀመ መሆኑን የመከታተል ስራ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።