← All news
News Nov 3, 2026 · 4d ago

ደቡብ ወሎ የተቀሰቀሰው ውጊያ‼️

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ሀይሎች መካከል ካለፉት አምስት ቀናት ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።ይህንን ውጊያ ተከትሎ የደሴ-ወልዲያ መንገድ ከትናንት ጀምሮ እንደተዘጋ ታውቋል፡፡ በውጫሌ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያዎችና በድሮን የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል። ትናንት ሰኞ በከተማዋ ልዩ ሥሙ "ዳንካ ሚካኤል" በተባለ ሥፍራ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙና ሆኖም በወቅቱ በንጹሃን ላይ የደረሠ ጉዳት ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ለመናገር እንደማይችሉ ነዋሪዎቹ ገልጸውልናል። በሌላ በኩል፤ በሀብሩ ወረዳ ውርጌሳ እና ጊራና ገጠራማ አካባቢዎችም በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጊያ መቀጠሉን ተረድተናል፡፡