የአሜሪካ ጦር በኢራኗ ቃሽም ደሴት ላይ ‹‹የመከላከል››ጥቃት ማድረሱ ተዘገበ
የአሜሪካ ጦር በኢራኗ ቃሽም ደሴት ላይ ‹‹የመከላከል››ጥቃት ማድረሱን የሀገሪቱን ባለሥልጣን ጠቅሰው የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ባለሥልጣኑ ተናገሩ ተብሎ እንደተጠቀሰው፤ ‹‹ይህ እርምጃ ኢራናውያን በአሜሪካ የጦር ሀብቶች ላይ ከመሬት ወደ አየር የሚተኮሱ ሚሳዔሎችን በመጠቀማቸው የተወሰደ የመከላከል እርምጃ ነው››ብለዋል። መጀመሪያ በ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል የተዘገበው ይህ ጥቃት የተፈጸመው፥ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዛሬዉ የፓርላማ አጋማሽ ምርጫ በኋላ ከኢራን ጋር አዲስ ከፍተኛ የጦርነት ግጭት ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ስጋት ለማቃለል ባሰቡበት ወቅት ነው። ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፥ከኢራን ጋር ጦርነት ነበረን፤ አሸንፈናል። ላለፉት ወራት ምንም አይነት ውጊያ ሳናደርግ ስለቆየን እንደ ጦርነት እንኳ ትቆጥሩታላችሁ ብዬ አላስብም ብለዋል። ነገር ግን የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን ኢላማዎች ላይ ለአያሌ ሳምንታት አነስተኛ መጠን ያላቸውን ጥቃቶች ሲፈጽሙ ቆይተዋል። እንደ ዘገባው ከሆነ፣ አንዳንዶች የአሜሪካ ባለሥልጣናት እነዚህ ክዋኔዎች ኢራን ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በሚያልፉ የንግድ መርከቦች ላይ ስጋት የመፍጠር ወይም ጥቃት የማድረስ አቅም እንዳታገኝ ለመከላከል ታስበው የተደረጉ ናቸው ብለዋል።