በሕገወጥ መንገድ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ዘጠኝ ሕፃናትን ስታዘዋውር የነበረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጠምባሮ ልዩ ወረዳ ወደ ወልቂጤ ከተማ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ዘጠኝ ህፃናትን በሕገወጥ መንገድ በቤት ሠራተኝነት ለማስቀጠር ስታዘዋውር የነበረች ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውላለች ሲል ፖሊስ ገልፇል። አብዛኞቹ ቤተሰቦች በድህነት ምክንያት ልጆቻቸው ቤተሰቡን እንዲደግፉ በማሰብ ለተጠርጣሪዋ የሰጧቸው ቢሆንም፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ ከትምህርት ገበታ ተነጥለው ለሥራ መዘጋጀታቸው ሕገወጥ ነው ተብሏል። ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ለጠምባሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ያስረከበ ሲሆን፣ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል። ሕፃናቱ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል የተባለ ሲሆን ወደ ትምህርት ገበታቸውም እንዲቀላቀሉ መደረጉም ተገልፇል።