በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 3መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 3መቶ64 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 3መቶ60 ወንዶች፣ 4ቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ፤ከተመላሾች መካከል 18ቱ ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል። ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሠራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ1መቶ12 ሺህ 5መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም ገልጿል።