← All news
News Nov 2, 2026 · 5d ago

በትግራይ ከጥቅምት 30 ጀምሮ የመንግሥት

ሠራተኞች ደመወዝ ሊከፈል ነው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከጥቅምት 30 ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንደሚከፈል አሳወቀ። የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ አረጋይ እንደገለጹት፤ በሥራ ገበታቸው ተገኝተው ሪፖርት ላደረጉ እና በሕጋዊ መንገድ ለሚሠሩ ሠራተኞች ክፍያው የሚፈጸም ሲሆን፣ ለዚህም አስፈላጊው የፋይናንስ ዝግጅት ተደርጓል። ይህ እርምጃ በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ሥራዎችን በድጋሚ ለማስጀመር እና የሠራተኞችን ተነሳሽነት ለመገንባት የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል። በትግራይ ያሉ ሠራተኞች ለረጅም ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው በመቆየቱ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግርና ውድቀት ተጋልጠው እንደነበር ይታወሳል።