← All news
News Nov 2, 2026 · 5d ago

በትራፊክ አደጋ አምስት የሳፋሪኮም ሠራተኞች ህይወት አለፈ።

በምእራብ ኦሮሚያ ዞን ዲጋ ወረዳ በደረሠ የትራክ አደጋ አምስት የሳፋሪኮም ሠራተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።   የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮምንኬሽን እና ሚዲያ ክፍል ሐላፊ ምክትል ኮማንደር ስሜነሽ አለማየሁ እንደገለፁት ጥቅምት21ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ላይ አደጋው ደርሷል። የሰሌዳ  ቁጥር ኮድ 3-60348 ኢቲ የሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ለሲሚንቶ ምርት የሚያገለግል ጥቁር የከሠል ድንጋይ ጭኖ ከአርጆ ጉደቲ ከተማ በመነሳት ወደ ነቀምቴ ከተማ ሲጓዝ ከነቀምቴ ከተማ አምስት የሳፋሪኮም ሠራተኞችን የጫነ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-A-42651 አዲስ አበባ የሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ ጋር ጉደቱ አርጆ የተባለ ቦታ በመጋጨታቸው የተከሠተ አደጋ መሆኑን ገልፀዋል።   በዚህ የተሽከርካሪ ለተሽከርካሪ ግጭት የፒካፑን አሽከርካሪ ጨምሮ በፒካፕ ተሽከርካሪ ውስጥ ያሉ አምስቱም የሳፋሪኮሞ ሠራተኞች ሕይወታቸውን ማጣታጣቸውን ገልፀዋል። በአጋጠመው ከባድ የተሽከርካሪ አደጋ ሶስት ሴቶች እና ሁለት ወንዶች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን በአደጋው ከፍተኛነት የተነሣ የፒካፑ ተሽከርካሪ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ስሜነሽ አለማየሁ ጨምረው ገልፀዋል።