← All news
News Nov 2, 2026 · 6d ago

አስገራሚ እውነታዎች ስለእንቅልፍ

• የሰው ልጅ የዕድሜውን አንድ ሦስተኛ የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው። ይህም በአማካኝ 25 ዓመት ይሆናል። • በቀን ከ7 ሰዓት በታች መተኛት የሰዎችን አማካኝ የመኖሪያ ዕድሜ ይቀንሳል። • አላርም (የሚያነቃ ሰዓት) ከመፈጠሩ በፊት እንግሊዝ እና አየርላንድ ውስጥ ሰዎችን ከእንቅልፍ በመቀስቀስ የሚተዳደሩ ሠራተኞች ነበሩ። ሠራተኞቹ ማልደው ተነስተው በር እያንኳኩ ደምበኞችን ከእንቅልፍ ያስነሱ ነበር። • ቀንድ አውጣ ያለማቋረጥ ለ3 ዓመት መተኛት ይችላል። • ድመቶች የዕድሜያቸውን 70 በመቶ የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ድመቶች በቀን እስከ 16 ሰዓት ይተኛሉ። • አሜሪካን ለ1 ቀን ብቻ ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ዴቪድ አቹሰን፤ ከ24 ሰዓት የስልጣን ዘመናቸው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፉት በእንቅልፍ ነበር። ጊዜውም እ.ኤ.አ መጋቢት 4 ቀን 1894 ነው። • ማይግሬን (ከባድ የራስ ምታት)፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት እና የእንቅልፍ መቆራረጥ፣ የቅዥት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው። • በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፓል ከርን የተባለ የሀንጋሪ ወታደር የፊት ግንባሩን በጥይት ተመቶ እንቅልፍ የሚቆጣጠረው የአይምሮው ክፍል ላይ ከባድ ጉዳት ይደርስበታል። በዚህም ወታደሩ ለ40 ዓመታት ያህል (ቀሪ ዕድሜውን) ያለ እንቅልፍ አሳልፏል። • ቀጭኔዎች ንቁ ለመሆን በቀን ከ5 እስከ 30 ደቂቃ ብቻ መተኛት በቂያቸው ነው። ቀጭኔዎች በቀን በአማካኝ እስከ 5 ሰዓት ይተኛሉ። • ሞርፊን የሚለው ቃል የመጣው ሞርፈስ ከተባለው የጥንት ግሪኮች የእንቅልፍ እና የህልም አምላክ ነው። ሞርፊን የከባድ በሽታዎች የህመም ማስታገሻ ሲሆን በታማሚዎች ላይም የእንቅልፍ ስሜት ይፈጥራል። • ምሽት ላይ ካፌን ያላቸው እንደ ቡና ፤ ሻይ እና ኮካ ያሉ (የሚያነቃቁ) መጠጦችን መጠጣት ፤ አይምሯችን ሜላቶኒን የተባለውን የእንቅልፍ ሆርሞን የሚለቅበትን ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል። ይህም መደበኛውን የእንቅልፍ ስርዓት በአማክኝ እስከ 40 ደቂቃ ድረስ ያዛባል። •  የመተኛት ፍርሃት ሶምኒ ፎቢያ ይባላል። • አብዛኛው ሰው አልጋ ላይ ከወጣ በኃላ በ7 ደቂቃ ውስጥ እንቅልፍ ይወስደዋል። •  ስራን በወቅቱ የማይሰሩ ሰዎች ለእንቅልፍ ችግር (ኢንሶምኒያ) የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው። •  በተደጋጋሚ በነውጥ (ሁከት) የተሞሉ ህልሞችን ማየት፤ እንደ ፓርኪንሰን (የሚያንቀጠቅጥ በሽታ) እና ድሜንሻ (የመርሳት በሽታ) ያሉ የአይምሮ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል። •  ህልም እያዩ ህልም መሆኑን መረዳት እና የህልሙን ትዕይንት በተወሰነ መልኩ መቆጣጠር መቻል ሉሲድ ድሪም ይባላል። በተለይ ቪዲዮ ጌም መጫወት የሚያዘወትሩ ሰዎች እንዲህ አይነት ህልሞችን በተደጋጋሚ ያያሉ። • ከ80 በላይ በሳይንስ የተለዩ የእንቅልፍ ችግሮች አሉ። • የዓለም ህዝብ ቁጥር አንድ የእንቅልፍ መስተጓጎል ምክንያት ኢንተርኔት ነው። • ከመተኛታችን ከ2 ሰዓት በፊት ቴሌቭዥን ማየት እንዲሁም ስልክ እና ኮምፒዩተር መጠቀም እንቅልፍ ያስተጓጉላል። • የሰው ልጅ በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት የሚያሳልፈው ህልም በማየት ነው። • ዳክዬዎች የሚተኙት አንድ አይናቸው ሳይከደን ነው። • ስሉዝ የተባሉት እንስሳቶች 80 በመቶ የሚሆነውን የዕድሜያቸውን ከፍል የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ዓለም ላይ ቁጥር አንድ እንቅልፋም እና ዘገምተኛ እንስሳቶች ስሉዝዎች ናቸው። • ከየብስ እንስሳቶች በሙሉ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያላቸው ዝሆኖች ናቸው። ዝሆኖች በቀን እስከ 2 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ። • በእንቅልፍ ልብ የሚበሩ ወፎች አሉ። በተለይ ስደተኛ ወፎች (ወቅት እየጠበቁ ከሀገር ሀገር የሚጓዙ) አየር ላይ ለአጭር ጊዜ ያሸልባሉ።