← All news
News Nov 1, 2026 · 6d ago

እስራኤል በሶማሌላንድ ኤምባሲ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠች‼️

የእስራኤል አምባሳደር ማይክል ሎተም (Michael Lotem) በሶማሌላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ፣ በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት፣ ለፕሬዚዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ የሹመት ማረጋገጫ ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል። የሹመት ማረጋገጫውን ተከትሎም በሀርጌሳ ለሚገነባው የእስራኤል ኤምባሲ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። ይህ እርምጃ እስራኤል ታኅሣሥ 26፣ 2025 ሶማሌላንድን እንደ ነፃ ሀገር እውቅና ከሰጠች በኋላ፣ የሁለቱን ወገኖች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ቋሚ ተቋማዊ ትብብር ለማሸጋገር የተወሰደ እርምጃ ነው።