← All news
News Nov 1, 2026 · 6d ago

በአረካ ከተማ የኤቲኤም ካርዶችን በመስረቅ ገንዘብ ሲያወጣ የነበረ ግለሰብ ተያዘ

በአረካ ከተማ የተለያዩ ባንኮችን የኤቲኤም ካርዶች ከሕብረተሰቡ በመስረቅ ገንዘብ ሲያወጣ የነበረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአረካ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ሞሮጫ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው አቶ ሃብታሙ ከበደ የተባለው ግለሰብ፣ ሰዎች በኤቲኤም ገንዘብ በሚያወጡበት ወቅት ተገልጋይ በመምሰል የምስጢር ቁጥራቸውን እና ካርዳቸውን በመስረቅ ወንጀሉን ሲፈጽም መቆየቱን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንጂነር እሽቱ ፎላ ገልጸዋል። አዛዡ እንዳሉት፣ ግለሰቡ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ባንኮችን የኤቲኤም ካርዶች በመጠቀም ገንዘብ ሲያወጣ ቆይቷል። ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ከሕብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት፣ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት በአረካ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያወጣ ተይዟል። የፖሊስ አዛዡ ሕብረተሰቡ መሰል ወንጀሎችን የሚፈጽሙ አካላትን በመጠቆም ለፖሊስ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ግለሰቡን ለመያዝ በክትትልና በጥቆማ ድጋፍ ያደረጉትን አካላት አመስግነዋል።