← All news
News Nov 1, 2026 · 6d ago

በአዲስ አበባ ቀጨኔ አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

ትናንት ጥቅምት 21,2019 ዓ.ም ከኩዩ ወደ አዲስ አበባ እያመራ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ መሪውን በመሳቱ መጀመሪያ እግረኞችን ገጭቶ፣ በመቀጠልም ከውሃ ቦቴ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ተከስቷል። ​በቦታው ላይ እግረኛውን ጨምሮ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ በአጠቃላይ በ11 ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። ​ የሚኒባሱ አሽከርካሪ በአደጋው ጉዳት ደርሶበት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል። ​ አዲስ አበባ ፖሊስ አደጋውን "አሰቃቂ" ሲል ገልጾ፣ አሽከርካሪዎች የመንገድ ደህንነት ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ አሳስቧል። የአደጋው ትክክለኛ መንስኤም እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።