← All news
News Nov 1, 2026 · 7d ago

የአዲስ አበባ አነጋጋሪ ውሳኔ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ እጅግ አነጋጋሪ የሆነ ውሳኔ አሳልፏል። የተፈቀደን መሬት ከፋፍሎ የማጽደቅ ሙሉ እና ብቸኛ ስልጣን በከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠረጴዛ ላይ ብቻ እንዲወድቅ ካቢኔው  መወሰኑን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።  የዚህ የስልጣን ማዕከላዊነት ዋነኛ ምክንያት "ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት" የሚል ሽፋን ቢሰጠውም፣ የከተማዋን ውድ እና ስሱ ሀብት በአንድ ሹመኛ ብዕር ስር ማጠቃለሉ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ታዛቢዎችን እያነጋገረ ይገኛል። በቅርቡ በተደረገው የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ መዋቅራዊ ሹም ሽር፣ አቶ መኮንን ያይን በመተካት አዲሱ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመሆን የተሾሙት አቶ መላኩ ታምሩ ይህንን ግዙፍ ገቢ የመሰብሰብ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ይሁን እንጂ የመጨረሻው የመሬት ክፍፍል ማጽደቂያ ማኅተም ከቢሮው ኃላፊዎች አልፎ የከንቲባዋን ፊርማ ብቻ የሚጠብቅ ይሆናል።