← All news
News Nov 1, 2026 · 7d ago

14 ጊዜ ሎተሪ በማሸነፍ የሎተሪ ድርጅቶችን ግራ ያጋባው የሂሳብ ሊቅ

ስቴፋን ማንደል  የተባለ ሮማኒያዊ የሂሳብ  ባለሙያ  በአለም ላይ ሎተሪን 14 ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛ ሰው ነው። ስቴፋን ሎተሪን ያሸነፈው በእድል ሳይሆን በሂሳብ ቀመር ነበር። በዚያን ጊዜ የነበረውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ የፈለገው ስቴፋን፣ የሎተሪ ጨዋታን እንደ አንድ የሂሳብ ችግር በመመልከት ጥናት ጀመረ። ከተወሰኑ ሙከራዎች በኋላም በመጀመሪያው ጥረቱ ሎተሪውን አሸንፎ ሕይወቱን የሚቀይር ትልቅ ሽልማት ወሰደ፤ ይህም ለቀጣዮቹ ትላልቅ ስኬቶቹ መሠረት ሆነለት። ስቴፋን የተጠቀመበት ዘዴ ከቀላል ዕድል በጣም የራቀ ነበር። የሎተሪውን ሕግጋትና ሊወጡ የሚችሉትን ቁጥሮች በሰፊው ካጠና በኋላ፣ ሊወጡ የሚችሉትን ሁሉንም አማራጮች ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቲኬቶችን በአንድ ጊዜ በመግዛት አሸናፊነቱን በሂሳብ አስልቶ ያረጋግጥ ነበር። ይህንን ሥራ ለብቻው አልነበረም የሚሰራው፤ በርካታ ሰዎችን በማስተባበር «ቡድን» በማቋቋም ቲኬቶቹን በጅምላ ይገዛ ነበር። ሎተሪው ሲወጣም የሚያሸንፈው ገንዘብ ለወጪውና ለባለአክሲዮኖቹ ከሚከፈለው ክፍያ በላይ በመሆኑ ሁልጊዜም አትራፊ ነበር፡፡  ይህ ዘዴው አውስትራሊያን እና አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ተደጋግሞ በመሰራቱ  የሎተሪ ድርጅቶችንና መንግሥታትን ከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ ከቷቸዋል። ድርጅቶቹ አንድ ሰው በሂሳብ ቀመር ብቻ ሁልጊዜ ማሸነፍ መቻሉን ሲረዱ፣ የጨዋታውን ሕግ በመቀየር በጅምላ ቲኬት መግዛትን በሕግ አገዱ። ዛሬ ላይ ስቴፋን የተጠቀመበት ዘዴ በዓለም ዙሪያ የተከለከለ ቢሆንም፣ የሰው ልጅ አእምሮ ከዕድል በላይ በስሌት ምን ያህል አስገራሚ ነገሮችን መሥራት እንደሚችል የሚያሳይ ታሪካዊ ማሳያ ሆኖ ቆይቷል።