← All news
News Oct 31, 2026 · 7d ago

«ትብብር ለህልውና» የተሰኘው ኃይል በዛሬው ዕለት አድራሻውን ካልገለፁበት ቦታ መግለጫ መስጠቱን ተመልክተናል።

መግለጫው የተሰጠው ኤርትራ ሆነው እንደሆነ የተለያዩ ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ። መግለጫው አሁንም መንግስትን በኃይል ለመጣል ትግላችንን እንቀጥላለን የሚል ሲሆን ዶ/ር ደብረፂዮን ከአቶ ዘመነ ካሴ ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠው ታይተዋል። አቶ አማኑኤል አሰፋም በቦታው ታይተዋል።